አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር።
የዝግጅቱ መጠናቀቅና የግብይት ማስጀመሪያ መርሐ ግብርን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሃብረቢ የስምምነቱ ትግበራ ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የግብይት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑንም ጠቁመዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በየብስ ትራንፖርት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ እንደሚላክ አብራርተዋል፡፡
አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ስምምነት ትግበራ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት ጠቁመው÷ ለሀገር ውስጥ ንግድ ተወዳዳሪነትና ኢንቨስትመንት መነቃቃት፣ ለሸማቹ የተሻለ አማራጭና ሰፊ የምርት አቅርቦት እንዲሁም በአፍሪካ ሀገራት መካከል የገበያ ትስስርን ለማስፋት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል፡፡
በቤተልሔም መኳንንት
አስተያየት ለመስጠት እባክዎ ይግቡ።
fffffff