በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ… ካሊድ በሽር

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ… ካሊድ በሽር
mifta juneidi Sep 17, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡


እንደ ኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ ተማሪ ካሊድ በሽር እንግሊዘኛ 96፣ ሒሳብ 100፣ ፊዚክስ 100 ኬሚስትሪ 98፣ ባዮሎጂ 99፣ አፕቲትዩድ 98 አምጥቷል፡፡


የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ደቱ ዲቦ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ተማሪ ካሊድ በሽር በትምህርቱ በጣም ጎበዝ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው እና አርአያ የሆነ ተማሪ ነው፡፡


በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱ መደሰታቸውንም ገልጸዋል፡፡


በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ከ50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት ያለፉት፡፡


50 ት/ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ሲሆን ÷1 ሺህ 249 ት/ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም፡፡


አስተያየት ለመስጠት እባክዎ ይግቡ።

እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። አስተያየት ለመስጠት የመጀመሪያው ይሁኑ!