አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዲስ ከተመረጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫው በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ በማድረጋቸው ለሕዝበ ሙስሊሙና ለምክር ቤቱ አመራሮች አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።
የመጅሊስ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ መከናወኑ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም አመልክተዋል።
መንግሥት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ የሚሠራ ሲሆን÷ በሚያስፈልገው ሁሉ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ጠቁመዋል።
ለምክር ቤቱ አመራሮች መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።
አስተያየት ለመስጠት እባክዎ ይግቡ።
እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። አስተያየት ለመስጠት የመጀመሪያው ይሁኑ!