አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል በሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ አትሌቲክ ቢልባኦን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ አርሰናል አትሌቲክ ቢልባኦን በሜዳው እና በደጋፊዎቹ ፊት ነው 2 ለ 0 ያሸነፈው፡፡
በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ከባድ ፉክክር የገጠማቸው መድፈኞቹ ከእረፍት መልስ ተቀይረው የገቡት ማርቲኔሊ እና ትሮሳርድ ባስቆጠሯቸው ግቦች አሸንፈዋል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1፡ 45 ላይ በተካሄደ ጨዋታ ፒ ኤስ ቪ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በዩኒየን ሴንት ግሎዥ ተሸንፏል።
የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቤኔፊካ ከካራበርግ፣ ጁቬንቱስ ከዶርትሙንድ፣ ሪያል ማድሪድ ከማርሴ እና ቶተንሃም ከቪያሪያል ይጫወታሉ።
አስተያየት ለመስጠት እባክዎ ይግቡ።
እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። አስተያየት ለመስጠት የመጀመሪያው ይሁኑ!