ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሰራተኛው የስራ ባህል እና በቀጣይ ስራዎች

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሰራተኛው የስራ ባህል እና በቀጣይ ስራዎች
Ziyad Ahmed Oct 17, 2025

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሰራተኛው የስራ ባህል እና በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ከተቋሙ የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።


የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የሰራተኛዉን የስራ ባህል እና  የቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ ከተቋሙ የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄዷል።


የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተዉፊቅ ጀማል የአስተዳደር ሰራተኞች ተቋሙ የሚመራባቸውን የስራ መመሪያዎች በመተግበር የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።


ሰራተኛው ባለፈው ዓመት ተቋሙን በባለቤትነት ስሜት እና በቁርጠኝነት በማገልገሉ የተመዘገበውን ውጤት እንደመነሻ በመውሰድ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የተሻለ መትጋት አለበት ብለዋል።


የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት መ/ርት አለዊያ ሀሰን በበኩላቸው እንደተቋም የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሁሉንም ሰራተኛ የስራ ባህል በተሻለ መልኩ ማዳበር እንደሚያስፈልግ ገልጸው ለዚህ ደግሞ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።


የአስተዳደር ሰራተኞች በበኩላቸው ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በማሻሻል እና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ውጤታማ ስራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


አስተያየት ለመስጠት እባክዎ ይግቡ።

እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። አስተያየት ለመስጠት የመጀመሪያው ይሁኑ!