ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራት ብቸኛው መድሃኒት መደመር ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
mifta juneidi
Sep 17, 2025
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራት ብቸኛው መድሃኒት መደመር ነው አሉ።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመጽሐፉ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራት ዋነኛው ጉዳይ መከፋፈል ነው ብለዋል፡፡
መከፋፈል የኢትዮጵያውያን ሃሳብ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠላቶች አጀንዳ መሆኑን ገልጸው፥ መለያየትን ለማስቀረት እንደመራለን ነው ያሉት፡፡
የጠላቶቻችን አጀንዳ ዘር፣ ሃይማኖት፣ መንደር፣ ጾታእየተባለ እኛን መለየት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የዚህ መፈወሻ ብቸኛው መድሃኒት መደመር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ስንደመር ታሪክ እንደምንሰራ ከጥንት ጀምሮ ስለሚታወቅ ስለመደመር ስናስብ ጠላቶቻችን ይደነግጣሉ ብለዋል።
በጋራ በመቆም መፍጠንና መፍጠር እንዲሁም በአስፈላጊው ቦታ ደግሞ በመዝለል ከተቀባይነትና ከተከታይነት መላቀቅ እንችላለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ገንዘብ እና ተልዕኮ ተቀብሎ ኢትዮጵያ ላይ መለማመድ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሰውን ሃሳብ ከሀገር ጥቅም አንጻር የማንመዝንና የምንሰማው ሁሉ ትክክል ነው ብለን ለመመረመር የማንዘጋጅ ከሆነ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንቸገራለን ነው ያሉት።
ኢትዮጵያውያን በተቀመጠብን የስነ ልቦና ስብራት ምክንያት አንችልም ብለን በመቀበላችን ጥሩ ነገር ስንመለከት እኛ ነን የሰራነው ብለን ለመቀበል ይከብደናል ብለዋል።
ለዚህ የኢትዮጵያ ስብራት ፈውስ የሚሆነው ብቸኛው መድሃኒት መደመር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በሶስና አለማየሁ
አስተያየት ለመስጠት እባክዎ ይግቡ።
እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። አስተያየት ለመስጠት የመጀመሪያው ይሁኑ!